
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ ክቡር አባ ተስፋዬ ታደሰን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ጳጳስ ብለው መሰየማቸውን ቫቲካን ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም. አወጀ።
ክቡር አባ አባ ተስፋዬ ታደሰ ዘማኅበረ ኮምቦኒ በመስከረም 12, 1962 ዓ.ም. ( 22/09/1969 እ.ኤ.አ.) በሐረር ከተማ የተወለዱ ሲሆን ከተወለዱ ከጥቂት ወራት በኋላ ወደ ቤተሰባቸው የመኖሪያ ከተማ ወደ አዲስ አበባ መጡ።በአዲስ አበባ ከ 1ኛ እስከ 8ኛ በሰፈራቸው በነበሩት ትምህርት ቤቶች በምስራቅና በነጻነት ብርሃን ትምህርት ቤቶች የተማሩ ሲሆን፣ ከ9ኛ ክፍል እሰከ 12ኛ በቦሌ አጠቃላይ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተምረዋል።…..