
ስለ ቤተክርስትያናችን
ልደታ ማርያም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በቶሮንቶ
ልደታ ማርያም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በቶሮንቶና በአካባቢው የሚገኙ ካቶሊክ ኢትዮጵያዊያንን በዋናነት የምታገለግል ቤተክርስትያን ስትሆን የምትደዳረውም በቶሮንቶ ሃገረ ስብከት ስር ነው።
ክቡር አባ ኢሳያስ ዱላ መሪ ካህን ሆነው ለማገልገል ከመጡበት እና ቤተክርስቲያናችን ከተመሠረተችበት ከ2009 ጀምሮ ቤተክርስቲያናችን በመንፈሳዊ አገልገሎትና በምዕመናን ቁጥር እያደገች የመጣች ሲሆን የምዕመናን ምክር ቤቱም በውቅቱ መሪ ካህናችን ከሆኑት ከአባ ቢኒያም ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡
ቤተክርስቲያናችን በአሁኑ ወቅት በቶሮንቶ ከተማ ውስጥ ዉልቨርሊ ቡለቯርድ ላይ በምትገኘው በቅድስት ብሪጅድ ቤተክርስቲያን ከሚገኙ ካቶሊካዊያን ወንድሞችና እህቶች ጋር በመዳበል የተሟላ ቅዳሴና መንፈሳዊ አገልግሎት በመስጠት ላይ ትገኛለች።ለልጆቻችንም የካቶሊክን ስርዓት በተከተሉ መንፈሳዊ መርህ ታንጸው የሚያድጉበት አመቺ ቦታ ሆናለች፡፡
የቤተክርስቲያናችንም ዓመታዊ ክብረ በዓል (ልደታ ማርያም) በየአመቱ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ ከኤርትራዊያን ኪዳነ ምሕረት ካቶሊካዊያን ወንድሞችና እህቶች፣ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ወዳጆቻችንና እንግዶቻችን ጋር በመሆን በደመቀ ሁኔታ ይከበራል፡፡
ልደታ ማርያም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን በቶሮንቶ
300 Wolverleigh Blvd, Toronto, ON M4C 1S6, Canada
ስልክ ቁጥር:.(437) 258 4812 / ኢ-ሜይል: lmethiocatholic@gmail.com
በህዝብ ትራንስፖርት ለመምጣት
በቲቲሲ ሳብዌይ መስመር #2 (Bloor–Danforth) እስከ ዉድባይን ሰብዌይ ጣቢያ ድረስ ይሂዱ።
ከጣቢያው ይውጡና በዉድባይን አቨኑ ላይ ወደ ሰሜን አቅጣጫ Wolverleigh Boulevard እስከሚደርሱ ድረስ በእግር ይሄዱ (ከ3 እስከ 5 ደቂቃ)።
Wolverleigh Boulevard ሲደርሱ ወደ ግራ (ወደ ምዕራብ) ይዙሩና በተጨማሪ ለ5 ደቂቃ ያህል ይቀጥሉ — ቤተክርስቲያኑ በዚሁ መንገድ ላይ ይገኛል።